ከ20,000 የሚበልጡ የማኅበሩ በጎ ፈቃደኞችን በዲጂታል የትስስር ገፆች እንዲገናኙ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ገለፀ፡፡
የማዕከላዊ አካባቢ ጽ/ቤት 29ኛ አመታዊ ጉባኤውን በአዳማ ከተማ በ17/07/2014 ዓ.ም አካሂዷል፡፡ የማኅበሩ ዋና ስራ አሰኪያጅ አቶ ጌታቸው ሀብቴ በመልካምና አርቆ አስተዋይ በጎ ፍቃደኞች የተመሠረተው ማኅበር ለ56 ዓመታት የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ማኅበሩ የተዋልዶ ጤናን አገልግሎት በሀገሪቱ የጀመረ፤ መንግስት በጤና ኤክስቴሽን ኘሮግራሙ የሚሠጠውን አገልግሎት በህብረተሰብ አቀፍ ጤና አገልግሎት ሰጭ በጎ ፍቃደኞች መነሻ …