
የኢትዩጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር ዓለማቀፍ የወሊድ መከላከያ ቀንን በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የተዋዶ ጤና አገልግሎት መስጫ ክሊኒኮቹ አከበረ…………………………………………
ዓለማቀፍ የወሊድ መከላከያ ቀን በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ የኢትዩጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር የተዋዶ ጤና አገልግሎት መስጫ ክሊኒኮች ተከብሯል ይህንኑ ዓመታዊ ክብረ በዓል ስለወሊድ መከላከያ ማኅበረሰቡ የበለጥ ግንዛቤ አግኝቶ አገልግሎቱ በስፋት እንዲዳረስ እና ተጠቃሚዎችም ስለወሊድ መከላከያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የመማማሪያ መድረክ ተፈጥሯል በዚሁ መድረክ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፤ ተወካዩች፤ የሀይማኖት አባቶች ፤ አባ ገዳዎች፤ ወጣቶች ፤ እናቶችና የልዩ ፍላጎት ተጠቃሚዎች የፕሮግራሙ ተሳታፊ ሆነዋል::












የኢትዮጵያ ቤተሰብ ምሪያ ማኅበር ላለፉት 60 ዓመታት የቤተሰብ እቅድ አገልግሎትን በመስጠት ፈር ቀዳጅ በመሆን ዛሬም የተጠቃሚዎችን ግንዛቤ ከማሻሻል በተጨማሪም ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት ረገድ ከፍተኛውን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ “እንቅፋቶችን መስበር፣ ድልድዮችን መገንባት፡ ለሁሉም ብቁ ለሆኑ ሁሉ የወሊድ መከላከያ ተደራሽነት!” በሚል መሪ ቃል የተከበረው የዓለም የወሊድ መከላከያ ቀን በአዲስ አበባ፤ በመቀሌ፤ በአክሱም፤ በባህር ዳር ፤ በጎንደር፤ በሐረር፤ በድሬዳዋ፤ በጅግጅጋ፤ በጅማ፤ በሐዋሳ፤ በአዳማ፤ እንዲሁም ደሴ በሚገኙ ሞዴል ክሊኒኮች ፤ ወጣት ማዕከላት እና መካከለኛ ተዋልዶ ጤና ክሊኒኮቹ በተለያዩ ዝግጅት በዓሉን በድምቀት አክብሯል ። ተሳታፊዎቹም በጥያቄና መልስ ፕሮግራሙ ላይ በሰጡት አስተያየት ስለ ወሊድ መከላከያ ምርጫዎች ጥልቅ ግናዛቤ እንዲኖርና የተለያዩ አፈ ታሪኮችንና የተሳሳቱ አመለካከቶችን ያስወግዳል ብለዋል ጨምረውም ተደራሽነትን ለማስፋትና ያልተሟሉ ፍላጎቶችን ለማሟላት ጠንካራ አጋርነትን ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ ይኸው አሳታፊ የነበረው የአለም የወሊድ መከላከያ ቀን በባለሙያ ትምህርት ፤ በድራማና ሙዚቃ ልዩ ዝግጅት፤ በጥያቄና መልስ እንዲሁም በባለ ድርሻ አካላት መልዕክት ቀኑ ተከብሯል፡፡