የG+3 ሁለገብ ህንፃ የፊኒሽንግ ስራ (Finishing labor work)

  የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር

አዳማ የሚገኘውን የG+3 ሁለገብ ህንፃ የፊኒሽንግ ስራ (Finishing labor work) በጉልበት / በባለሙያ ዋጋ ብቻ (Labor Cost Only) መስራት የሚችሉ ድርጅቶችን ለማወዳደር በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር ለትርፍ ያልተቋቋመ የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለማዳረስ በ1958 ዓ.ም. የተመሠረተ መንግሥታዊ ያልሆነ የህክምና አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ነው፡፡ አዳማ የሚገኘው የማኅበሩ ማእከላዊ አካባቢ ፅ/ቤት ከተዋልዶ ጤና ክሊኒኩ አጠገብ ባለው ቦታው ላይ ያስገነባውን G+3 ሁለገብ ህንፃ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የማጠናቀቂያ ስራዎች (Finishing Works) በእጅ / በጉልበት ዋጋ ብቻ (Labor Cost Only) መስራት የሚችሉ ኮንትራክተሮችን  አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ የግንባታው ማጠናቀቂያ ስራዎቹም (Finishing Works)

  • CARPENTRY AND JOINERY          . PAINTING WORK
  • ALUMINUM WORK                   . SANITARY INSTALLATION
  • FINISHING WORK                   . ELECTRICAL INSTALLATION

ስለሆነም ከላይ በተገለፀው መሰረት በአዳማ ከተማ ምንጃር ጎዳና ትልቁ መስጊድ አካባቢ በሚገኘው የማህበሩ ክሊኒክ አጠገብ የተገነባውን G+3 ሁለገብ ህንፃ የማጠናቀቂያ ስራዎችን (Finishing Works) በእጅ/በጉልበት ዋጋ ብቻ (Labor Cost Only) ለመስራት ለመወዳደር የምትፈልጉ ከደረጃ 6 (ስድስት) በላይ የሆናችሁና መስፈርቱን የምታሟሉ ህንፃ ተቋራጮች ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን ሠነድ አዲስ አባባ ዋናው መ/ቤት እና አዳማ በሚገኘው ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በማይመለስ ብር 20ዐ.ዐዐ በመግዛት በጨረታው እንደትወዳደሩ እንጋብዛለን፡ተጫራቾች

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፤
  2. ቫት የተመዘገቡና የቫት ሰርተፍኬት ወይም ቲኦቲ፤ የታክስ ክሊራንስ ሰርፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
  3. ተጫራቾች ለዚሁ ስራ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሠነድ አዲስ አበባ የሚገኘው የማኀበሩ ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዳማ በሚገኘው ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በመቅረብ በመግዛት የሚችሉ
  4. ተጫራቾች የፋይናንስና የቴክኒካል ፕሮፖዛላቸውን ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ሞልተው ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በማድረግ ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት እንደዚሁም ብር 50000 የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ለብቻው ካሸጉ ቡሃላ ሁሉንም ሰነዶች በአንድ ትልቅ ፖስታ ከተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቁያው በሪፖርተር ጋዜጣ የአማርኛ እትም ከወጣበት ከመስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ረቡእ መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር ዋናው መ/ቤት ማስገባት ይችላሉ፤
  5. ጨረታው ረቡዕ መስከረም 25 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ተዘግቶ ለመገኘት በፈቀዱና በተገኙ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት በእለቱ ከሰአት ቡሃላ በ7፡3ዐ ስዓት ይከፈታል፡
  6. ማኀበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተከበረ ነው፡፡

አድራሻ

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኀበር

ፖ.ሳ.ቁጥር 5716

ስልክ ቁጥር ዐ1146723ዐዐ አዲስ አበባ ወይም 0221111303 አዳማ

አዲስ አበባ -ሪቼ መስከረም ማዞሪያ 2ዐዐ ሜትር ገባ ብሎ ወይም አዳማ ከሪፍትቫሊ ሆቴል ፊትለፊት በኦይል ሊቢያ ገባ ብሎ

Scroll to Top