የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር የስራ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

ማኅበሩ እ.ኤ.አ 2021 የ1ኛ ሩብ ዓመት በዋናው መስሪያ ቤትና በስምንት አካባቢያዊ ጽ/ ቤቶች የተከናወኑ የሶስት ወራት የስራ ዕቅድ እና አፈፃፀሞችን ግምገማ ከግንቦት 7 – 8/2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ቱሊፕ ሆቴል አካሂዷል፡፡

በግምገማው ላይ የተሳተፉት ከዋናው መ/ቤት እና ከአባቢያዊ ጽ/ቤቶች የመጡ ሃላፊዎችና ሰራተኞች በስራ ዕቅዱና አፈጻጸም ላይ ጥልቀት ያላቸውን ግምገማዎችና ገንቢ ሃሳቦችን አንሸራሽረዋል፡፡ በስራ አፈጻጸም ሂደቱ የታዩ ጠንካራ የስራ አፈጻጸሞች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ዝቅ ያሉ የስራ አፈጻጸሞች ደግሞ በቀሪዎቹ ጊዚያቶች ሙሉ ትኩረት በመስጠት የታለመው ግብ እውን ለማድረግ እንዲሰራ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

Scroll to Top