ቤተሰብ መምሪያ ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ ስድስት ሚሊዮን ሰዎችን ሊያስተናግድ ነው

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር፣ በተያዘው
የፈረንጆች ዓመት ለሚያስተናግዳቸው 6.1 ሚሊዮን
ተጠቃሚዎች ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት
መመደቡን ይፋ አደረገ::
የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር 25ኛ መደበኛ
ስብሰባ ባለፈው ቅዳሜ በግዮን ሆቴል ሲያካሂድ፣
ያለፈውን ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምና የዚህን ዓመት
ዕቅድ የዳሰሱ ሪፖርቶች ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን
ከሪፖርቶቹ ለመረዳት እንደተቻለው፣ ባለፈው ዓመት
ለ5.4 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች በቤተሰብ ዕቅድ ላይ
ያተኮሩ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ተሰጥቷቸዋል::
አምና ለተከናወኑት አገልግሎቶች ማስፈጸሚያ
167 ሚሊዮን 621 ሺሕ 867 ብር ተመድቦ 99
ከመቶ ያህሉ በሥራ ላይ የዋለ ሲሆን ለዚህ ዓመት
አገልግሎት ማከናወኛ ደግሞ 152 ሚሊዮን 465 ሺሕ
537 ብር በጀት ተይዟል::
ማኅበሩ ከተለያዩ ረጂ ድርጅቶች ጋር እያደረገ ባለው
ግንኙነት ተጨማሪ በጀት እያገኘና የፕሮጀክት ስምምነት
እየተፈራረመ በመሆኑ ማኅበሩ የሚያንቀሳቅሰው የዚህ
ዓመት አገልግሎት በጀት ከተጠቀሰው መጠን ሊጨምር
እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ ተዘጋጅቷል ተብሏል::
ሆኖም የዘንድሮው በጀት ካምናው ዝቅተኛ ሆኖ
ይታያል:: በአንፃሩ አገልግሎት ይሰጣቸዋል የተባሉተ
ሰዎች ቁጥር ከ700 ሺሕ በላይ ጭማሪ አሳይቷል::
ማኅበሩ በቅርቡ በዋናው መሥሪያ ቤት የተዋልዶ
ጤና ሪፈራል ክሊኒክና ማሠልጠኛ ማዕከል ሥራ
ለማስጀመር የሕንፃው የውስጥ ሞዲፊኬሽንና
ግንባታውን ለክሊኒክና ለማሠልጠኛ ማዕከሉ
የሚያስፈልጉ ዕቃዎችም በመሟላት ላይ ይገኛሉ::
ክሊኒኩ ሥራ እንዲጀምር ፈቃድ እየጠበቀ ሲሆን
የሥልጠና ማዕከሉ ግን ሥራውን ጀምሯል:: በቅርቡም
ሁለቱም በይፋ ይመረቃሉ ተብሎ ይጠበቃል::
እርምጃው የማኅበሩን አቅም የተሟላ ከማድረጉም
በተጨማሪ ለኅብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት
ቀጣይነት ይበልጥ እንዲያጠናክር ያደርገዋል ተብሏል::
ወ/ሮ መዓዛ ቅጣው የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ፣
የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበር የሥነ ተዋልዶ
ጤና አገልግሎት ማሠልጠኛ ሆኖ የተመረጠው
ባለፈው ዓመት መሆኑን ገልጸዋል:: የመረጠውም
የዓለም አቀፍ ቤተሰብ ፌደሬሽን የአፍሪካ ሪጂን ነው::
ሊመረጥ የቻለው በአፍሪካ ከሳሃራ በታች ካሉ 42
የፌደሬሽኑ አባል አገሮች በአገልግሎት፣ በጥራትና
ጥንካሬው የተሻለ ደረጃ ላይ በመቀመጡ ነው::
ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ፌደሬሽን የአፍሪካ ቀጣና
በቦርዱ ሥልጣንና ተግባር፣ በመልካም አስተዳደር፣
በቦርድና በማኔጅመንተ ተገቢ የሥራ ግንኙነት፣
በማኅበሩ ጠንካራ የሥራ አመራርና ይዘት ትኩረት
ያደረገ የሦስት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት
ለማኅበሩ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት ሰጥቷል::
ከወ/ሮ መዓዛ ቅጣው ማብራሪያ ለመረዳት
እንደተቻለው፣ ማኅበሩ በዚህ ብቻ ሳይወሰን በመልካም
አስተዳደርና የማኔጅመት ሥራ ሒደት ላይ እንዲሟሉ
የሚጠየቁ መስፈርቶችን በማሟላቱ ከዓለም አቀፉ
የቤተሰብ ፌደሬሽን ለሁለተኛ ጊዜ የምስክር ወረቀት
አግኝቷል::
የማኅብሩ አወንታዊ የሥራ ውጤቶች ቢኖሩም
በዓመቱ ውስጥ ያጋጠሙትና ከበፊት ጀምሮ የነበሩ
ጎልተው የመጡ ችግሮች መኖራቸውን ፕሬዚዳንቱ
ጠቁመው፣ ብቁ ባለሙያ ይዞ ማቆየትም ሆነ አዳዲስ
ሠራተኞችን መሳብ አለመቻል አንዱ ችግር መሆኑን
ገልጸዋል::
በዚህም የተነሳ የተሟላና የሠለጠነ የባለሙያ ኃይል
ይዞ ሥራውን ለመምራት አስቸጋሪ ሆኗል:: በአሁኑ
ወቅት ማኅበሩ የሥራ መዋቅሩንና የደመወዝ ደረጃውን
የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ለመቅረጽ
እንዲቻል ሥራውን አማካሪ ድርጅት ሰጠቷል:: የጥናቱ
ውጤት በቀረበ ጊዜም በተግባር ለመተርጎም ተጨማሪ
የፋይናስ ድጋፍ የማግኘቱ ጉዳይ የሚያሳስበው ቢሆንም
ችግሩ እንዲቀረፍ ጥረት ያደርጋል ተብሏል::
የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማኅበርን በጋራ ሆነው
የማቋቋም ሐሳብ የጠነሰሱት በ1955 ዓ.ም. በአገሪቱ
የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት የታየውን ችግር ለመቅረፍ
መሥራት አለብን ብለው የተነሱ ጥቂት ፈቃደኛ
የማኅበረሰብ ሳይንስና ጤና ባለሙያዎች ናቸው:: በዚህ
የተነሳ ማኅበሩ የቤተሰብ ዕቅድ ግንዛቤ ለኅብረተሰቡ
የማስጨበጥ ተግባር ሲያከናውን ከቆየ በኋላ፣ በ1958
ዓ.ም. የሥነ ተዋልዶ ጤና መረጃ፣ የምክርና የክሊኒክ
አገልግሎቶች ፈቃደኛ ለሆኑና የቤተሰብ ቁጥራቸውን
ለመመጠን ለሚፈልጉ እናቶችና ወጣት ሴቶች መስጠት
ጀምሯል::
ማኅበሩ በአሁኑ ጊዜ 29 የሥነተዋልዶ ጤና
አገልግሎት መስጫ ክሊኒኮች፣ 28 የወጣት ማዕከላት፣
50 ፍራንቻይዝድ የግል ክሊኖኮችና ከ250 በላይ
የሚሆኑ በየገጠሩና በየከተማው የሚገኙ የአገልግሎት
መስጫዎች እንዳሉት፣ 172 የዓለም አገሮችን
በአባልነት ያቀፈው የዓለም አቀፍ ቤተሰብ ፌደሬሽን
አባል እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

Error | Family Guidance Association of Ethiopia

Error

Error message

  • The file could not be created.
  • PDOException: SQLSTATE[23000]: Integrity constraint violation: 1062 Duplicate entry '' for key 'uri': INSERT INTO {file_managed} (filesize, timestamp) VALUES (:db_insert_placeholder_0, :db_insert_placeholder_1); Array ( [:db_insert_placeholder_0] => 0 [:db_insert_placeholder_1] => 1496003862 ) in drupal_write_record() (line 6861 of /home2/gaeet/public_html/includes/common.inc).
The website encountered an unexpected error. Please try again later.